Login Here

Who is Online

We have 4 guests online
Home FIULI Project Office

የፌዴራል የተቀናጀ የከተማ መሬት መረጃ

ፕሮጀክት ጽ/ቤት

አጠቃላይ

መግቢያ

ከተሞች በመሬት ልማትና አስተዳደር የተጣለባቸውን ተግባርና ኃላፊነት ዘመናዊ፣ ውጤታማና ቀልጣፋ በሆነ ሥርዓት መወጣት እንዲችሉ በቅድሚያ የመሬትና መሬት ነክ ንብረቶች ምዝገባና መረጃ አያያዝ መተግበር አስፈላጊ ሆኗል፡፡

የመሬት ምዝገባና መረጃ ሥርዓቱ የመብት ምዝገባ እንደመሆኑ በካርታ የተደገፈ እንዲሆንና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት መዘርጋትና የወቅቱን ቴክኖሎጂ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ይህ ሥርዓት የቴክኖሎጂ ስታንደርድ ወጥቶለት፣ ደረጃውን የጠበቀና ወጥ በሆነ መልኩ በከተሞች ለመተግበርና የላቀ ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የከተሞች የመሬት መረጃ ሥርዓት ዝርጋታውን በቅርበት የሚከታተልና የሚደግፍ የፕሮጀክት ጽ/ቤት በፌደራል ደረጃ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ስር እንዲቋቋም አስፈልጓል፡፡

ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ዋነኛ ተግባር በየከተሞች ለሚቋቋሙ የመሬትና መሬት ነክ ምዝገባና መረጃ ሥርዓት ፕሮጀክት ጽ/ቤቶች የቴክኒክ ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን የከተሞቹ ፕሮጀክቶች ራሳቸውን ችለው እስኪቆሙ ወይም እስከሚጠናቀቁ የሚያግዝ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የሚኒስቴር መ/ቤቱ፣የክልልና የከተማ የመሬት ነክ ተቋማት ለሚያደራጁት የመሬት ዳታ ቤዝ አያያዝና ቅብብሎሽ ተመሳሳይ የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

የጽህፈት ቤቱ መቋቋም የቴክኖሎጂ ስታንደርድ ለማስቀመጥ፣ ከከተሞች ጋር በጋራ ቴክኖሎጂ በመመረጥና ግዢ በማከናወን ወጥ አሰራር እንዲኖር ለማድረግ እንዲሁም ከአገር ውስጥ (ከክልሎችና ከተሞች) እና ከውጭ አገር የሚገኝን ምርጥ ተሞክሮ ለመቀመርና ለማስተላለፍ ያግዛል፡፡