Login Here

Who is Online

We have 2 guests online
Home FRPR Agency About the Agency

የፌደራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

1. መግቢያ

ሃገራችን ኢትዮጵያ ካሏት ከፍተኛ ሀብቶች መካከል የሰው ጉልበት፣ እና የተፈጥሮ ሃብት መሆኑ ተጠቃሽ ነው፡፡ በተለይ መሬት ለዜጎች ካለው ከፍተኛ ፋይዳ አንጻር በቀደሙት አመታት የመሬት ማኔጅመንት የአሠራር ችግሮች ሲዳሰሱ በኢኮሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጽእኖ ያሳረፋበት፣ ውስብስብና አስቸጋሪ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የመሬት አስተዳደር የፈጠረው አሉታዊ ተጽእኖ በመነሻነት ስንመለከተው በአደረጃጀት፣ እርስ በርሳቸው የማይናበቡና አገራዊ የጂ.ኦደ.ቲክ መቆጣጠሪያ መረብን ስታንዳርድ ለመጠበቁ ማረጋገጫ አለመኖሩ፣ በየጊዜው የመረጃዎች ለውጥን ተከትሎ አለመያዙ፣ የከተማ ልማት ማኔጅመንት ፖሊሲ አለመኖሩ፣ የህግ ማዕቀፎች ገቢራዊ የሚያደረግ ተቋማዊ አተገባበር ያለመኖር፣ የመሬት መረጃው ሥርዓቱን ጠብቆ አለመዘርጋቱ፣ መረጃዎቹ ምንም አይነት የደህንነት ከለላ የሌላቸው ሃገራዊ ወጥነት ያለው አመራር፣ አሠራርና አደረጃጀት የመሳሰሉትን በርካታ ችግሮች ይዞ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡

መንግሥት በዘርፋ ላይ ያሉትን ተጠቃሽ የአሠራር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ስትራተጂ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የመሬት ማኔጅመንቱን የአሠራር ችግር በአንፃራዊ መልኩ እውቀትን መሠረት ያደረገ፣ ቴክኒክና ቴክኖሎጂን አስተሳስሮ በማልማት ወደ ዘመናዊ አሠራር ማስገባት እንዲቻል ታስቦ ለሕብረተሰቡ የመሬት ባለቤትነት ሥርዓት ማበጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት የፌዴራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ተቋም በአዋጅ ሊቋቋም ችሏል፡፡

2. የፌ/የከ/////// ኤጀንሲ የተቋቋመበት አብይ ምክንያት

መንግሥት በሃገራችን የተዘበራረቀውን የከተማ የመሬት አስተዳደር አሠራር ሥርዓት ለማስጠበቅና የመሬት አስተዳደር ወቅቱ በሚፈልገው መጠን አዘምኖ እንዲጓዝ ሃገራዊ ተልዕኮ እንዲኖረው በተለያየ መልኩ የዳሰሳ ጥናት አካሂዷል፡፡ በመሆኑም የፌደራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በሃገር አቀፍ ደረጃ በማስተባበር ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ሥርዓት እንዲዘረጋ ለማስቻል እንዲሁም የፌደራል የከተሞች የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ መረጃ ማዕከል ሆኖ እንዲሰራ በመንግስት ተወስኖÿል፡፡ በዚህ መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በተሰጠው ስልጣን መሠረት ïዴራል ነጋሪት ጋዜጣ 17 ዓመት ቁጥር 85 ሐምሌ 13/2003 .. ባወጣው ደንብ ቁጥር 251/2003 መሠረት ïዴራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ተቋቁሟል፡፡

3. የኤጀንሲው ሥልጣንና ተግባር

1. የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረትን ለመመዝገብ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችንና ህጎችን ያመነጫል፣ የማስፈጸሚያ ስልቶችን ይነድፋል፣ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን የምዝገባና የሕጋዊ ካዳስተር ደረጃዎች እንዲወጡ ያደርጋል፣

2. መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ሥርዓት ይዘረጋል፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ መለያ ኮዶች ሥርዓት ያወጣል እንዲሁም የመለያ ኮዶቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ በከተሞች ተጣጥመው ተፈጻሚ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣

3. የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና የመሬት ይዞታን ለማረጋገጥ የወጡ ህጎች፣ፖሊሲዎች ደረጃዎችና የአሠራር ሥርዓቶች በተገቢው ሀኔታ በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣

4. ïዴራልና የክልል ከተሞች የምዝገባ ተቋማትን በማስተባበር በቴክኖሎጂ የተደገፈና ወጥ የሆነ የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ የመረጃ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ïዴራልና በክልል ተቋማት መካከል ደረጃውን የጠበቀ የሚናበብና ቀጣይነት ያለው የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፣ መረጃውን ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል፣

5. የካዳስተር ባለሙያዎች ስልጠና ኘሮግራም ስለሚስፋፋበትና የሙያ ብቃት የሚረጋገጥበት ሥርዓት ስለሚጠናከርበት ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፣

6. በከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት አመዘጋገብና በመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጥናት በመለየትና ተገቢውን መፍትሄ በመፈለግ የምዝገባ ሥርዓቱ ቅልጥፍና ያረጋግጣል፣

7. የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባን የሚያከናውኑ ተቋማት እንዲያደራጁ ለክልል ከተሞች ድጋፍ ያደርጋል፣ ተቋማቱ ደረጃውን የጠበቀ ምዝገባ ለማከናወን እንዲችሉም የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ይሠራል፣

8. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል ይከሰሳል፣

9. ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

4. የፌዴራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አደረጃጀት

/ቤቱ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ለመወጣት የመቋቋሚያ ደንቡን መሠረት በማድረግ ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ ያለው ድርጅታዊ መዋቅር መሠረት ኤጀንሲው አንድ ዋና ዳይሬክተር፣ ሦስት /ዋና ዳይሬክተሮች እና ሌሎች አራት ድጋፍ ሰጭ የሥራ ዘርፎችን ይዞ ተደራጅቷል፡፡

1. በእቅድ የተከናወኑ ግቦቹ እና አፈፃፀም በተመለከተ፤

Ø የኤጀንሲውን የሰው ኃይል ለማሟላት በቅጥር፣ በዝውውር ወይም በምደባ ከተለያዩ መሰል ተቋማት እንዲሟሉ እየተደረገ መሆኑ፣

Ø የአስተዳደርና ፋይናንስ ደይሬክቶሬት የሰው ኃይል ቅጥር በአብዛኛው እየተሟላ ይገኛል፣

Ø የኤጀንሲውን ሥልጣንና ተግባር እንዲሁም ተልዕኮ አዲስ ለተቀጠሩ የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

Ø ተቋሙ የቁሣቁስ ግዥ ለማከናወን ለመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አቅርቦ ያልተስተናገዱትን የግዥ ዕቅድና ስልት እንዲፀድቅ አብሮ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

Ø ለኤጀንሲው አገልግሎት የሚውል ተሽከርካሪ በዘላቂነት የሚገኝበትን ሁኔታ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ጥያቄ በማቅረብ የጉዳዩን ተፈጻሚነት በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡

Ø የተቋሙ መጠቀሚያ የሆነ አዲስ ህንፃ የሚገነባበት ቦታ እና የህንፃ ዲዛይን እንዲዘጋጅ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር እና የመከላከያ ኰንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ጋር በጋራ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

2. በቀጣይ በትኩረት የሚከናወኑ ጉዳዮች፡

Ø ከክልሎች ጋር ተከታታይ ግንኙነት በመፍጠር ሥራዎች ወደ ክልል ከተሞች መውረዳቸውን ማረጋገጥና ያሉትን ዝግጁነቶች የመፈተሽ ሥራ  በመስክ በመገኘት በተከታታይ መፈጸም፣

Ø ተቋሙን በማስተዋወቅ በመንግስት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ዘንድ ተገቢው ግንዛቤ እንዲዳብር በማድረግ በቂ ድጋፍ የማግኘት አጋጣሚዎችን መፍጠር፤

Ø በከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት መብት ምዝገባ ሥርዓት ዙሪያ ባለሙያዎች፣ መሠል የክልል ተቋማት የትምህርት ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት እና ተግባራዊ የሚያደርጉት/ተጠቃሚ አካላትን በወርክ ሾፕ፣ በውይይትና በምክክር ወዘተ… ግንዛቢያቸው እንዲዳብር ብሎም የህዝብ ንቅናቄ እንዲፈጠር ማድረግ፣

Ø የፌደራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ባለሙያዎችን መሠል የክልል ተቋማትን በተቋሙ ፕሮግራም እና በከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ፖሊሲ ዙሪያ፣ በካዳስተር ስታንደርድ እንዲሁም የህግ ማእቀፎች ዙሪያ ሥልጠና መስጠት፡፡

Ø የተጓደሉ ኤጀንሲው የማደራጀት ሥራዎች ዙሪያ የማጠናቀቅያ ሥራ ማከናወን፡፡

Ø የክልል የኤጀንሲ ተቋማትን ማጠናከር እና የከተሞችን ምዝገባ ተቋማት በማደራጀቱና የማገዝ ሥራ በመስክና ከማዕከል እገዛ ማድረግ፡፡

Ø ከክልሎች በሚመጡት ሪፖርቶች ዙሪያ የመስክ ግምገማ ማድረግ፤

Ø በ23 ከተሞች የሚሰሩትን የካዳስተር መሰረታዊ ካርታ ሥራ እና የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦች መስፋፋት ሥራ ዙሪያ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ወደ ውጤት ማድረስ፣

Ø ከአዲስ አበባ፣ መhሌ፣ አዳማ እና ሐዋሳ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመሬት አስተደደር ዙሪያ የሰው ኃይል ልማት እንዲካሄድ የፍላጎት ግምገማ እና የካሪኩለም ቀረፃ እንዲካሄድ በማድረግ፣ የመሬት አስተዳደር ትምህርት ክፍል እንዲቋቋም ማድረግ፣

Ø ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር በጋራና በመደጋገፍ በሁለት ወረዳዎች ላይ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት መብት የማረጋገጥና ምዝገባ የማካሄድ ሥራን በማካሄድ ተሞክሮ መቀመር፣

Ø የክልል የመሬትና መሬት ነክ ተቋማት እንዲቋቋሙ የሠነድ እና ሙያዊ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

Ø ከአዲስ አባ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ ለመሥራትና ባለሙያ ለማሠልጠን የመግባቢያ ሠነድ ፊርማ ተካሂዷል፡፡

Ø በክልል ከተሞች የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ተgም መጠቀሚያ የሚሆን ህንፃ ግንባታ ቦታ ዝግጅት በ23 ከተሞች ተከናውኗል፡፡

Ø 23 ከተሞች ላይ ነባር ሰነዶችን ለማደራጅት ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ ከክልል የከተማ ልማት ተቋማት ጋር ንግግር በማድረግ ትኩረት እንዲገኝ የማድረግ ሥራ በክትትል ላይ መሆኑ፣

Ø የከተማ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት መብት ምዝገባ አዋጅ ለክልሎች፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የህግ ተቋማት፣ የንግድ ምክር ቤቶች እና የፋይናንስ ተቋማት እንዲደርሳቸው ተደርጐ ግብአታቸውን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፡፡

Ø በክልል ደረጃ የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በማቋቋም ላይ በጋራ መስራትና የሚጠየቁ ድጋፎችን መስጠት፣