Login Here

Who is Online

We have 4 guests online
Home ULDM Bureau About the Bureau

የከተማ መሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ

 

1. መግቢያ

የከተማ መሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ የከተማ መሬት ልማት እና ማኔጅመንት ስርኣትን በዘላቂነት በመቀየር ዘርፉ ለከተሞች ልማት እና መልካም አስተዳደር ግንባታ ተገቢዉን ሚና መጫወት እንዲችል በአግባቡ ለመምራት በግንቦት 2003 ዓ.ም. በስሩ ሶስት መምሪያዎችን በማዋቀር በአዲስ መልክ የተቋቋመ ነዉ፡፡

እነዚህም መምሪያዎች፡-

· የመሬት ልማት እና ከተማ ማደስ መምሪያ

· የመሬት ግብይት እና አስተዳደር መምሪያ

· የከተማ መሬት መረጃ መምሪያ ናቸዉ፡፡

1.1. የቢሮዉ ዓላማ

ዘመናዊ እና ዉጤታማ የከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት የከተሞች ልማት፤ዕድገት እና መልካም አስተዳደር ስኬት እዉን እንዲሆን ማስቻል፤

1.2. የቢሮዉ ተልዕኮ

በሁሉም የሀገራችን ከተሞች በ2010 ዓ.ም. የተሟላ፤ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ፤ቀጣይነት ያለዉ የመሬት አቅርቦት፤ደረጃዉን ጠብቆ መልሶ የታደሰ የከተማ አካባቢ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ የመሬት ልማት እና አስተዳደር አሰራር እና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ተረጋግጦ ማየት፤

2. የቢሮዉ ተግባራት እና ኃላፊነቶች

2.1. የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን መቅረጽ ሲጸድቁም አፈጻጸማቸዉን መከታተል፤

2.2. የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ህጎችን መቅረጽ ሲጸድቁም አፈጻጸማቸዉን መከታተል፤

2.3. ቀልጣፋ እና ተናባቢ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት አደረጃጀት ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ጥናቶችን በማከናወን አፈጻጸማቸዉን መከታተል፤

2.4. በከተሞች የደቀቁ እና ያረጁ አካባቢዎች መልሶ ለማደስ የሚያስችሉ ዉጤታማ እና አዋጭ አማራጮችን በማጥናት ተግባራዊነታቸዉን መከታተል፤

2.5. በከተሞች የተሟላ እና ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ኢኮኖሚያዊ የመሬት ዝግጅት አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን፤

2.6. በከተሞች ዘመናዊ፤ ቀልጣፋ፤ግልጽ እና ፍትሀዊ የመሬት ግብይት እና አሰተዳደር ስርዓት ለማስፈን የሚያስችሉ ዉጤታማ አሰራሮችን በማጥናት ተግባራዊነታቸዉን መከታተል፤

2.7. በከተሞች ብቁ የሆነ የመሬት ሀብት ቆጠራ፤ምዝገባ እና ጠንካራ የመረጃ ስርዓት ለመፍጠር የሚያስችል አቅም መገንባት፤

3. ቢሮዉ ያከናወናቸዉ እና በማከናወን ላይ የሚገኙ ተግባራት

3.1. ቢሮዉ ያከናወናቸዉ ዋና ዋና ተግባራት

3.1.1. የከተማ መሬት ልማት እና ማኔጅመንት ፖሊሲ እና የአፈጻጸም ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

3.1.2. የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት አደረጃጀት በማጥናት ከፌደራል እስከ ከተሞች እንዲናበብ ተደርጓል፡፡ በዚሁ መሰረት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተሞች የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት በቢሮ ደረጃ ራሱን ችሎ የተዋቀረ ሲሆን በክልሎች በክልል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ስር በአዲስ መልክ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

3.1.3. የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የሚያስችል አዋጅ 721/2004 ተሻሽሎ በተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እና ጸድቆ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

3.1.4. የሊዝ አዋጁን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ሞዴል ደንብ እና ሞዴል መመሪያ እንዲሁም ዝርዝር ማኑዋል ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

3.1.5. የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን መሰረት በማድረግ በዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራትን በመለየት በዕቅድ ተይዞ እና ከክልሎች እና ከተሞች ጋር እንዲናበብ ተደርጓል፡፡

3.1.6. በዘርፉ ላይ በወጡ ፖሊሲ፤ህጎች እና ማኑዋሎች ላይ በዘርፉ ላይ ለሚገኙ ፈጻሚዎች፤አመራሮች እና የሚመለከታቸዉ አካላት ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡

3.2. በመከናወን ላይ የሚገኙ ዋና ዋና ተግባራት

3.2.1. የመሬት ልማት እና ዝግጅት ማኑዋል፤ የከተሞች የተቀናጀ የመልሶ ማልማት አፈጻጸም ማኑዋል፤ የኢንዱስትሪ ቀጠና ልማት ማኑዋል፣

3.2.2. የከተሞች የመሬት ዝግጅት ፋይናንስ አማራጭ ስትራቴጂ፣

3.2.3. የዘመናዊ የከተማ ማዕከል ግንባታ ጥናት፣

3.2.4. የሶስተኛ ደረጃ ከተሞች የካዳስተር ስርዓት ዝርጋታ ጥናት፡፡